Obtenez 3 mois à 0,99 $/mois + 20 $ de crédit Audible

OFFRE D'UNE DURÉE LIMITÉE
Page de couverture de እንወያይ

እንወያይ

እንወያይ

Auteur(s): DW
Écouter gratuitement

À propos de cet audio

በሣምንቱ በተከሰቱ በዋናነት የኢትዮጵያ እንደ አስፈላጊነቱ የዓለም ዐበይት ፖለቲካዊ፣ ኤኮኖሚያዊ እና ማኅበራዊ ጉዳዮች ላይ ዶይቼ ቬለ ጉዳዩ በቀጥታ የሚመለከታቸውን በመጋበዝ ውይይት ይካሔዳል። በውይይቱ የመንግሥት ባለሥልጣናት፣ የተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮች፣ በተለያዩ ዘርፎች የተሰማሩ ባለሙያዎች ይጋበዛሉ። በየሣምንቱ እሁድ የሚተላለፈውን የዶይቼ ቬለ የውይይት መሰናዶ በየትኛውም የፖድካስት ምርጫዎን በምታገኙባቸው መንገዶች ማድመጥ ትችላላችሁ።2025 DW Politique Sciences politiques Sciences sociales
Épisodes
  • ውጥረት ያነገሰው የሰሞንኛው የህወሓት ታጣቂዎች እንቅስቃሴ እና ያስከተለው ስጋት
    Nov 16 2025
    የኢትዮጵያ ፌደራል መንግሥትና ህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) ፕሪቶሪያ-ደቡብ አፍሪቃ ላይ ግጭትን የማቆም ስምምነት ከተፈራረሙ ባለፈዉ ጥቅምት 23 ሶስኛ ዓመቱን አስቆጥሯል። ሶስቱ ዓመታቱ ብዙዎች እንደሚሉት ሁለቱ ኃይላት በስምምነታቸው መሰረት ግዴታቸውን ያልተወጡበት ወይም ሊወጡ ያልፈለጉበት ሰላምም ግጭት ያልነበረበት ሆኖ ነው ያለፈው።
    Voir plus Voir moins
    46 min
  • የኢትዮጵያ የውጭ ምንዛሪ ገበያ እና ብር ወዴት እያመሩ ነው?
    Nov 9 2025
    የውጭ ምንዛሪ ግብይት በአቅርቦት እና ፍላጎት እንዲወሰን ከተደረገ ወዲህ ኢትዮጵያ ከሸቀጦች የወጪ ንግድ የምታገኘው ገቢ ዕድገት ቢያሳይም ብር እየተዳከመ ነው። የወርቅ ኤክስፖርት መሻሻል ብር እንዲረጋጋ ሊያደርግ እንደሚችል ብሔራዊ ባንክ ተስፋ አድርጓል። የፕራግማ ኢንቨስትመንት አድቫይዘሪ ዋና ሥራ አስፈጻሚ መርዕድ ብሥራት፣ የፋይናንስ ባለሙያው ዶክተር አብዱልመናን መሐመድ እና ከፍተኛ የኢኮኖሚ ጉዳዮች አማካሪ የሆኑት ዶክተር ቀልቤሳ መገርሳ የተሳተፉበት ውይይት የምንዛሪ ገበያው ብር ላይ ያሳደረውን ተጽዕኖ ይፈትሻል።
    Voir plus Voir moins
    41 min
  • መፍትሄ ያጣው ግጭትና የልማት እንቅስቃሴ በኢትዮጵያ
    45 min
Pas encore de commentaire