Obtenez 3 mois à 0,99 $/mois + 20 $ de crédit Audible

OFFRE D'UNE DURÉE LIMITÉE
Page de couverture de የዓለም ዜና

የዓለም ዜና

የዓለም ዜና

Auteur(s): DW
Écouter gratuitement

À propos de cet audio

ዶይቼ ቬለ የዕለቱን ዋና ዋና ዜናዎች ከኢትዮጵያ እና ከመላው ዓለም በየቀኑ ያቀርባል። የኢትዮጵያ እና የአፍሪካ ፖለቲካዊ እና ኤኮኖሚያዊ ጉዳዮችን ጨምሮ የመላው ዓለምን ውሎ የተመለከቱ ጠቃሚ መረጃዎች በሰባቱም የሣምንቱ ቀናት ከምሽቱ አንድ ሰዓት ከዶይቼ ቬለ ያድምጡ። የዶይቼ ቬለን ዜናዎች በአፕል ፖድካስት እና በስፖቲፋይ ማድመጥ ትችላላችሁ። የዶይቼ ቬለ ዜና በራዲዮ፣ በሳተላይት እና በፌስቡክ በየዕለቱ በቀጥታ ይደመጣል።2025 DW Politique
Épisodes
  • የህዳር10 ቀን 2018 ዓ.ም. የዓለም ዜና
    Nov 19 2025
    የህዳር 10 ቀን 2018 ዓ.ም. አርዕስተ ዜና «ትብብር ለኢትዮጵያ አንድነት» በሚል መጠሪያ የተቀናጁት 5 ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች የኢትዮጵያ መንግስት ከምርጫው በፊት በሀገሪቱ ሰላም እና መረጋጋት እንዲያሰፍን ጠየቁ። ከኤርትራ መሆንዋ ተነገረ የአንዲት እናት የተቆረጡ እጆችን አውራ ጎዳና ላይ ማግኘቱን የጀርመን ፖሊስ ዐሳወቀ። በቦንየተገን ጠያቂዎች ማቆያ የትኖር የነበረው ይህች እናት፣ የት እንዳለች እስከ ትናንት ድረስ እንደማያውቅ ፖሊስ ገልጿል። በሱዳን ጦርነት ጣልቃ በመግባት የምትጠረጠረው የተባበሩት አረብ ኤሜሬቶች በማኅበራዊ መገናኛ ዘዴዎች የሚደርስባት ወርጂብኝ ተጠናክሮ ቀጥሏል። ሰ
    Voir plus Voir moins
    11 min
  • የዓለም ዜና፤ ኅዳር 9 ቀን 2018 ማክሰኞ
    Nov 18 2025
    አርስተ ዜናዎች፤ -ኢሕአፓ ባለፉት 7 ዓመታት በትግራይ ክልል ፣ በአፋር ክልልና በአማራ ክልል፣ አሁን ደግሞ በመላው የአማራ ክልልና በበርካታ የኦሮሚያ ክልል ቀጠናዎች ውስጥ፣ እየደረሱ ያሉ ያላቸውን የወገን ዕልቂትና የመሠረተ ልማት አውታሮች ብሎም የሌሎች ቋሚና ተንቀሳቃሽ ንብረት ውድመት እንዲቆም ዛሬ ባወጣዉ መግለጫ ጠየቀ።-የሩሲያ ጦር በስድስት የአፍሪቃ ሀገራት እየተንቀሳቀሰ መሆኑን የሩሲያ ቴሌቪዥን ዘገበ።-የጀርመን መንግስት የእስራኤል በከፊል አቋርጦት የነበረዉን የጦር መሳርያ አቅርቦት ዉሳኔ እንደሚያነሳ አሳወቀ። በሌላ በኩል የጀርመን ለዓለም አቀፍ የአየር ንብረት ጥበቃ ተጨማሪ 60 ሚሊዮን ዩሮ ሰጠች።
    Voir plus Voir moins
    11 min
  • የኅዳር 8 ቀን 2018 ዓም የዓለም ዜና
    Nov 17 2025
    ደቡብ ኢትዮጵያ ውስጥ ሦስት ሰዎች በማርበርግ ተሐዋሲ መሞታቸውን የጤና ሚኒስቴር አረጋገጠ። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በያዝነው ዓመት ለሚካሄደው 7ተኛው ጠቅላላ ምርጫ ፓርቲዎች ዕጩዎቻቸውን እንዲያስመዘግቡ ጥሪ አቀረበ። የባንግላዴሽ ልዩ ችሎት በቀድሞዋ የሀገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር እና የሀገር ውስጥ ሚኒስትሩ ላይ የሞት ፍድር በየነ። የፖሊስ አዛዡ ደግሞ አምስት ዓመት እስራት ተፈርዶባቸዋል። የሱዳን መንግሥት የተመ የሰብዓዊ መብቶች ምክር ቤት ዳርፉር አልፋሸር ውስጥ የተፈጸመውን ጥሰት የሚያጣራ ቡድን ለመላክ መወሰኑን ተቃወመ። በአንጻሩ ፈጥኖ ደራሹ ኃይል እውነቱን የሚያጣራው የልዑካን ቡድን እንዲላክ ጠይቋል።
    Voir plus Voir moins
    11 min
Pas encore de commentaire