Épisodes

  • የሐምሌ 10 ቀን 2017 ዓ/ም የዓለም ዜና
    11 min
  • የሐምሌ 9 ቀን 2017 ዓ.ም. የዓለም ዜና
    Jul 16 2025
    በአማራ ክልል ምዕራብ ጎጃም ዞን ደጋ ዳሞት ወረዳ ፈረስ ቤት ከተማ ትናንት በመንግሥት ኃይሎች እና በፋኖ መካከል ከፍተኛ ውጊያ እንደነበር ተሰማ። እራሱን እስላማዊ መንግሥት የሚለው ጽንፈኛ ቡድን አባላት መሆናቸው የተጠረጠ 82 ግለሰቦችን በቁጥጥር ሥር ማዋሉን የብሔራዊ የስለላና የደኅንነት አገልግሎት ዐሳወቀ። በአፋር ክልል አፍዴራ ከተማ ትናንት ምሽት የጣለዉ ብርቱ ንፋስ የቀላቀለ ዝናብ ለአንድ ሰዉ ሕይወት መጥፋት ምክንያት ሆነ፤ 31 ሰዎችም ተጎዱ። በሺህዎች የሚቆጠሩም ተፈናቅለዋል። የኬንያ መንግሥት ለበርካታ የአፍሪቃ እና የካሬቢያን ሃገራት የይለፍ ፈቃድ መስፈርቶችን አነሳ።
    Voir plus Voir moins
    10 min
  • የዓለም ዜና ፤ ሐምሌ 8 ቀን 2017 ማክሰኞ
    Jul 15 2025
    አርስተ ዜና፤ -የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ እንደ ቻይና እና ህንድ ባሉት የሩሲያ የንግድ አጋሮች ሸቀጥ ላይ እስከ 100 በመቶ የሚደርስ የትራፊ ጭማሪ እጥላለሁ አሉ። የሩሲያ ባለሥልጣናት ግን ይህ እርምጃ ጦርነቱን ከማስቀጠል በቀር ምንም የሚፈይደዉ ነገር የለም ሲሉ አጣጣሉት አጣጥላዋለች።-ድንበር የለሽ ሐኪሞች ድርጅት የተባለዉ ግብረ ሠናይ ድርጅት የዛሬ አራት ዓመት ትግራይ ክልል ዉስጥ ሆነ ተብሎ ስለተገደሉ ሦስት ባልደረቦቹ አሟሟት ያደረገዉን የዉስጥ ምርመራ ዉጤት ዛሬ በይፋ አሰራጨ።-በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ደቡብ ኦሞ ዞን ከ80 ሺህ በላይ ነዋሪዎች በኦሞ ወንዝ ሙላት መከባባቸውን ነዋሪዎች ገለፁ፡፡
    Voir plus Voir moins
    11 min
  • የሐምሌ 7 ቀን 2017 ዓ.ም. የዓለም ዜና
    Jul 14 2025
    የሐምሌ 7 ቀን 2017 ዓ.ም. አርዕስተ ዜና ሊቢያ ውስጥ በወሮበሎች ተይዘው ሲሰቃዩ የነበሩ ከ100 በላይ ስደተኞች ነጻ መውጣታቸውን ሊቢያ አስታወቀች።ከመካከላቸው 5 ሴቶች ይገኙባቸዋል። የአውሮጳ ኅብረት ከዋሽንግተን ጋር የሚያካሂደው የታሪፍ ንግግር ክልተሳካ 72 ቢሊዮን ዩሮ የሚያወጡ የአሜሪካን ምርቶች የታሪፍ ጭማሪ ዒላማ ሊሆኑ እንደሚችሉ አስጠነቀቀ። ባለፉት ሁለት ወራት ስፔን ውስጥ ከፍተኛ ሙቀት 1,180 ሰዎችን መግደሉን የሀገሪቱ የአካባቢ ሚኒስቴር አስታወቀ። እንደ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ እንዳለው ከሟቾቹ አብዛኛዎቹ እድሜያቸው ከ65 ዓመት በላይ ነው። ከግማሽ በላይ የሚሆኑት ደግሞ ሴቶች ናቸው።
    Voir plus Voir moins
    10 min
  • የሐምሌ 06 ቀን 2017 የዓለም ዜና
    Jul 13 2025
    ናይጄሪያ የሽብር እንቅስቃሴ በገንዘብ ይደግፋሉ ያለቻቸውን 44 የቦኮ ሐራም አባላት እስከ 30 ዓመታት በሚደርስ እስራት ቀጣች። በጋዛ ሕጻናትን ጨምሮ ውኃ ለመቅዳት በመጠባበቅ ላይ የነበሩ 10 ፍልስጤማያውን በተፈናቃዮች መጠለያ ውስጥ በእስራኤል የአየር ጥቃት መገደላቸውን የግዛቲቱ የሲቪል ሰዎች ደህንነት ጥበቃ ኤጀንሲ አስታወቀ። የሰሜን ኮሪያ መሪ ኪም ጆንግ ዑን ሩሲያ በዩክሬን ያለውን ግጭት ለመፍታት የምታደርገውን ጥረት ሀገራቸው “ያለ ምንም ቅድመ-ሁኔታ ለመደገፍ” ዝግጁ እንደሆነች ማረጋገጫ ሰጡ። ፕሬዝደንት ቮሎዶሚር ዜሌንስኪ ባለፈው አንድ ሣምንት ብቻ ሩሲያ በ1,800 ድሮኖች በዩክሬን ላይ ጥቃት እንደሰነዘረች ተናገሩ።
    Voir plus Voir moins
    9 min
  • የሐምሌ 5 ቀን 2017 ዓ.ም የዓለም ዜና
    Jul 12 2025
    የሐምሌ 5 ቀን 2017 ዓ.ም የዓለም ዜና በሲዳማ ክልል የሀዋሳ ዙሪያ ወረዳ ነዋሪዎች ለተቃውሞ አደባባይ ወጡ ፡፡ በኳታር አሸማጋይነት በእስራኤልና ሐማስ መካከል እየተካሄደ የነበረው ቀጥታዊ ያልሆነ የተኩስ አቁም ድርድር «በእስራኤል ተደራዳሪዎች እንቅፋት እየገጠመው ነው» ሲል ሐማስ ወቀሰ። ሩስያ ሌሊቱን ለዛሬ ቅዳሜ አጥቢያ በዩክሬይን ላይ ፈጸመችው በተባለ የድሮንና የሚሳይል ጥቃቶች ቢያንስ 2 ሰዎች መገደላቸውንና 14 መቁሰላቸውን ክዬቭ አስታወቀች።
    Voir plus Voir moins
    10 min
  • የሐምሌ 4 ቀን 2017 ዓ.ም. የዓለም ዜና
    Jul 11 2025
    የሐምሌ 4 ቀን 2017 ዓ.ም. አርዕስተ ዜና ሳዑዲ አረቢያ 2 ኢትዮጵያውያንን በሞት ቀጣች። የሳዑዲ አረቢያ የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስቴር ሁለቱ የኢትዮጵያ ዜጎች በሞት የተቀጡት አደንዛዥ እጽ በማዘዋወር ተከሰው መሆኑን ትናንት መናገሩን የፈረንሳይ ዜና አገልግሎት ዘግቧል።ኢትዮጵያውያኑ ሀሽሽ የተባለውን አደንዛዥ እጽ በማዘዋወር በፍርድ ቤት ጥፋተኛ ተብለዋል ። ከጎርጎሮሳዊው ግንቦት መጨረሻ ወዲህ በጋዛ እርዳታ ለማግኘት ከሞከሩ ሰዎች ወደ 800 የሚጠጉት እንደተገደሉ የተመድ ዛሬ አስታወቀ። አሜሪካን በተመድ ድርጅት ልዩ ባለሞያ ላይ ማዕቀቦች ለመጣል መወሰኗ ክፉኛ እንዳሳዘነው የአውሮጳ ኅብረት ዛሬ አስታወቀ።
    Voir plus Voir moins
    11 min
  • የዓለም ዜና፤ ሐምሌ 3 ቀን 2017 ዓ.ም ሐሙስ
    Jul 10 2025
    አርስተ ዜና፤ --የዩክሬይኑ ፕሬዚዳንት ዜሌንስኪ ሩስያ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰው አልባ አውሮፕላኖችንና ሚሳኤሎችን ትናንት ወደ ኪይቭ ዩክሬን ካስወነጨፈ በኋላ ሩስያ ላይ ጠንካራ ማዕቀብ እንዲጣል ጠየቁ።--በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ደቡብ ኦሞ ዞን ሳላማጎ ወረዳ ሦስት ሰዎች በአፈር ናዳ ተቀብረው ሕይወት አለፈ፡፡ --የኬንያዉ ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ «ስርዓት አልበኝነት» በቸልታ አይታለፍም ሲሉ ዝምታቸውን ሰበሩ። የሰዎችን ንብረት የሚያቃጥል እግሩ ላይ በጥይት ይመታል ፤ ህመሙ ሲያገግም ፍርድ ቤት እንደሚቆም ተናግረዋል።--የፍልስጤሙ ሽምቅ ተዋጊ ቡድን ሃማስ አስር የእስራኤል ታጋቾችን ለመልቀቅ መስማማቱ ተሰማ።
    Voir plus Voir moins
    10 min